EAII and SIMAD AI Institute Sign MoU to Strengthen AI Cooperation.
· MOU
EAII and SIMAD AI Institute Sign MoU to Strengthen Regional AI Research and Capacity Building
ስምምነቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መስክ ትብብርን ለማሳደግ በሶማሊያ ሲማድ ዩኒቨርሲቲ ስር ከተቋቋመው የሲማድ ኤ.አይ ኢንስቲትዩት ጋር የተደረገ ነው፡፡
በበይነ መረብ አማካኝነት የተካሄደው የፊርማ ሥነ-ስርዓት በሁለቱ ተቋማት መካከል በዘርፉ የትብብር አጋርነት ጅማሮ ማመላከቻ ነው፡፡
ስምምነቱ በአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ምርምር፣ ልማት እና የሰው ኃይል አቅም ግንባታ ማዕቀፎች ዙሪያ በጋራ ለመስራት ያስችላል፡
፡
በፊርማ ሥነ-ስርዓቱ ላይ የኢትዮጵያ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እንደተናገሩት ተቋሙ ከሲማድ ኤ.አይ. ኢንስቲትዩት ጋር በቅርበት ለመስራት እና በሁለቱ ሃገራት መካከል ልምድ እና አቅም ለመጋራት ቁርጠኛ መሆኑን ተናግረዋል። የመግባቢያ ሰነዱ ለመጪው ጊዜ ትብብር መነሻ መሆኑን እና ትርጉም ያለው የምርምር ውጤቶችን ዕውን ለማድረግ አቅም እንደሚሆን ገልፀዋል።
የሲማድ ኤ.አይ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ያህይ አቡካር (ዶ/ር) በበኩላቸው ትብብሩ ሁለቱ ተቋማት የጋራ ባህላዊ እና ቀጠናዊ ጥንካሬዎችን በመጠቀም ለሕብረተሰቡ ጠቃሚ የሆነ የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ መፍትሄዎችን እንዲያዘጋጁ ያስችላቸዋል ብለዋል። የሀገራቱን የእውቀት ሃብት እና ተሰጥኦ በማዋሀድ የአፍሪካ ቀንድ ለዓለማቀፉ የኤ.አይ ፈጠራ የራሱ አበርክቶ እንዲኖረው ያስችላል ሲሉ አመላክተዋል፡፡
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute