Meeting Held on AI Technology, Governance, Peace, and Security.
· Other
African Leaders Discuss AI Governance, Peace, and Security to Strengthen Economic Stability and Institutional Productivity in Africa.
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ዋና ዳይሬክተር ወርቁ ጋቸና (ዶ/ር) እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) ጨምሮ የአፍሪካ ህብረት ሰላም እና ጸጥታ ምክር ቤት ሚኒስትሮች የታደሙበት ስብሰባ በበይነ መረብ ተካሂዷል።
ውይይቱ “ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ፣ አስተዳደር፣ ሰላም እና ጸጥታ በአፍሪካ'' በሚል ርዕሰ ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው።
የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዎስ (ዶ/ር) በስብሰባው ላይ ባደረጉት ንግግር፥ ሰው ሰራሽ አስተውሎት ቴክኖሎጂ በዓለም አቀፍ ደረጃ የአስተዳደር፣ የኢኮኖሚ ልማት እና የደኀንነት ጉዳዮችን በፍጥነት እየለወጠ መሆኑን ተናግረዋል።
መንግሥታት እና ተቋማት በውሳኔ አሰጣጥ፣ በሕዝብ አስተዳደር፣ በደኀንነት ሥርዓት እና በኢኮኖሚ ዕቅዳቸው ሰው ሰራሽ አስተውሎትን በተቀናጀ መንገድ የመጠቀም ሁኔታቸው በከፍተኛ ደረጃ እየጨመረ መምጣቱን ሚኒስትሩ አንስተዋል።
የአርቲፊሻል ኢንተለጀንስ ቴክኖሎጂ አጠቃቀም በአግባቡ ካልተመራ ሐሰተኛ መረጃዎችን በማስፋፋት እና የሳይበር ወንጀሎችን በማበራከት ለሽብርተኛ
ድርጅቶች ብሎም በተባባሪዎቻቸው ጥቅም ላይ ሊውል እንዳይችል ለዘርፉ አስፈላጊውን የሕግ ማዕቀፍ ማበጀት እና ማጠናከር እንደሚገባ በስብሰባው ተነስቷል።
Source: Ethiopian Artificial Intelligence Institute